ፉክክር፣ ብሔረተኛነትና ትብብር በለውጡ ዋዜማ (ዩሱፍ ያሲን)

ፉክክር፣ ብሔረተኛነትና ትብብር በለውጡ ዋዜማ (ዩሱፍ ያሲን)

በማጠቃለያ የአፋር ዘማቾች የጦር ውጊያ ዝግጅታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በባሕሉ ከውጊያ ስምሪት በፊት ከትንቢት ተናጋሪዎች የሚጠብቁት ትንቢት አለ፡፤ ነቢይቷ ሴት ከሆነች “ባዲቶ” ወንድ ከሆነ ደግሞ “ግኒሊ” ይባላሉ፡፡ የመጨረሻ ስንብት ከማድረጋቸው በፊት የመጪውን ውጊያ ትንቢት እንዲነገራቸው የሚለዋወጡት “ምን ይታይሻል” “ምን ይታይሃል? “ቅኔ ዘረፋ ብጤ ታሪክ ልመርቅላችሁ። “ባዲቶ” ወይም ትንቢት ተናጋሪዋ እንዲህ በማለት ትጀምራለች” አዎ፣ ይታየናል ረጅሙ ለግላጋው ባለ ሎቲው ሲደናቀፍ.፣ ትቀጥልና ራሰ በራው ዘመዱ ላይ ላይ ሲወድቅ ፣ ታዋቂው ጀግናው ዉሃ ውሃ ሲል…. እያለች ዘማቹ ጦር መስማት የማይፈልገውን የወገን ኪሳራና ሟርት-አዘል ትንበያ ስታበዛባቸው ” ዝም በይ፣ አንቺ ቀባዣሪ፣ ውሸታም” እያሉ ከቀኝ ከግራ ዘማቾቹ ሲወራርፏት “ዮኦ ዲራብለ ሲኒህ አበይ ይ ራቦው” በማለት አሳርጋ ትሸኛቸዋለች። አባባሏ ወደ ቀላሉ አማርኛ ሲመለስ “ፈጣሪ አምላኬ፣ እኔኑ ውሽታም ያድርግላችሁ” ብላ ነው የምትጸልይላቸው። እኔ ትንተናየን በዚህ ሟርት እያሳረግኩ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ። ይታሰብበት! ነው መልእክቴ። የእጃችሁን አጣጥፋችሁ ተቀመጡ ጥሪም ግን በፍጹም አይደለም። የኃይል ሚዛን መለወጥ አለበት ብዬ የምደሰኩር ሰው ነኝ። እየተለዋወጠም ነው። እያየነው ነው። ስጋቴን ብቻ ያልደበቅኩበት በቂ ምክንያት አለኝ። ሥርዓትን ብቻ እንቀይራለን ብለው ተነሳስተው ባልጠበቁት ከፍተኛ አብዮት እንቅስቃሴ ትርምስምስ መሓል ሃገራቸውን ጭምር ያጡ ወገኖች (ሶሪያ፣ሊቢያ፣የመን፣ኢራቅ) እንደ መማማሪያና ልብ መግዣ እየተመለከትን ነው፡፡ ይህንን እያዬን ለምንስ አንፈራም! ። መማሪያ አታሳጣን እንጂ እኛኑ ለሌሎች መማማሪያ አታድርገን በማለት የዘወትር ጸሎታችንን አሁንም እናደርሳለን።እናንተም አድርሱ!

ፉክክር፣ ብሔረተኛነትና ትብብር በለውጡ ዋዜማ (ዩሱፍ ያሲን)

 

Leave a Reply

 

 

 

You can use these HTML tags

<a href="" title=""> <abbr title=""> <acronym title=""> <b> <blockquote cite=""> <cite> <code> <del datetime=""> <em> <i> <q cite=""> <s> <strike> <strong>